tamemfn Tamirat Tesfaye

ወቸው ጉድ! እያልኩ እተርካለሁ። ከእያንዳንዱ ጀርባ ድብቅ ሴራ አለ።


Kısa Hikaye Tüm halka açık.

#]
Kısa Hikaye
0
2.8k GÖRÜNTÜLEME
Devam etmekte
okuma zamanı
AA Paylaş

ከጀርባ

የሴራ ፖለቲካ (Conspiracy politics) በጣም መጥፎ ነገሩ የአንተ ያልሆነን ሥራ፣ የማይወክልህን፣ የማይመጥንህን ነገር ለጥፎ በህብረተሰብ ውስጥ ማሰራጨት ነው። እውነት የላቸውም። በውሸት ተደራጅተው እና አደራጅተው የሚፈልጉትን ያደርጋሉ። ይኸ ለረጅም ዘመናት ለህዝባችን ያልጠቀመ ከጫንቃችን ላይ አሽቀንጥረን መጣል ያለብን የረከሰ ያረጀ ስልት ነው። ሴራ ለህዝብ አይጠቅምም። ግለሰቦችንና ውስን ቡድንን ያደልባል። ኢትዮጵያ ይኸንን ሥርዓት ለመቅረፍ አድስ የለውጥ ጉዞ ላይ ናት። እውነተኛ ዲሞክራሲ፣ ሀሳብ በልጦ የሚገዛበትን ሥርዓት እየዘረጋን ነው።


በግሌ እኔን የማይመጥን እና የማይገልጸኝን ሥም ስሰጡኝ ዝም ብዬ አላልፍም። እውነቱን ፍንትው አድርገ እናገራለሁ። እውነት ውሎ አድሮ ይገለጣልና። አሁን የታምራት ጉድለት ተብለው የተጠቀሱ 6 ነጥቦች አሉ።


ነጥብ 1.

"በመ/ቤቱ ሰፊ የመልካም አስተዳደር መኖሩና ችግሮችን ለመፍታት የአቅም ማነስ።"


የመልካም አስተዳደር ችግር የሚባሉት የባለሙያ ቅረታ፣ የተገልጋይ ቅረታ፣ የሌብነት ችግር፣ የሥራ አለመፈጸም፣ የሥነምግባር ችግሮች ናቸው። መስሪያ ቤቱን በኃላፊነት ስረከብ የተቋሙ ማናጅመንት እንኳን ፈርሶ ነበር። የመስሪያ ቤቱ አመራሮች እና ባለሙያ በጠላትነት የሚተያዩ ነበሩ።


በተረከብኩ ሣምንት ውስጥ አድስ የሥራ መንፈስ እና አደረጃጀት በመስራት ባለሙያዎች ህዝባቸውን ለማገልገል በወኔ ተነሳስተው ወደ ሥራ ገብተዋል። አድስ ዕቅድ አቅደው ያለ ክፊያ አቅራቢያ ቀበሌያትን በመደገፍ ሞደል አርሶ አደር ለመፍጠር ተሞክሯል(ከኋላ በአስቸኳይ ይቁም ተብሎ ሌላ የፖለቲካ መልክ ተሰጠው)። ይኸ ተሞክሮ መቀመር ያለበት ተግባር ነው። በሌላ በኩል አርሶ አደሩን ወርዶ ለመደገፍ የበጀት ማነቆ ስለነበረ መረጃዎችን ለማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነበር። ችግሩን ለመቅረፍ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤትና ከኢትዮ ተሌኮም ጋር በመናበብ ባለገመድ ስልክ ማስገባት ተችሏል።

0464670558(ኤክስቴንሽን ኮሙዩኒኬሽን ላይ)

0464670486(የዋና ኃላፊ ቢሮ)

4mb wifi አገልግሎት በመሆን መስሪያ ቤታችን መረጃዎችን መለዋወጥ እንድችል ተደርጓል።


የደረጃ ዕድገት፣ የደመወዝ ጭማሪ፣ ውዝፍ ክፊያዎች ሙሉ በሙሉ ምላሽ አግኝተዋል። ከ2009 ጀምሮ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች ላይ የነበረ የመድኃኒት ገንዘብ ዕዳ ነበር። ይኸ በየግዜው ኦድት ባለመደረጉ የወዘፈ ነው። ቢሆንም መስሪያ ቤታችን ባለሙያዎችን ጠርቶ በማወያየት ከነበረው ዕዳ 70% ተመላሽ ሆኗል። ባለሙያዎም ደስተኞች ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ። እኔ መስሪያ ቤቱን ከተረከብኩ ወዲህ በተሰራ ሪፎርም አንድም በዕዳ ውስጥ የገባ ባለሙያ የለም።

28 Mayıs 2021 23:29 2 Rapor Yerleştirmek Hikayeyi takip edin
1
Devam edecek...

Yazarla tanışın

Tamirat Tesfaye I am Tamirat Tesfaye. I appreciate people who wrote a story

Yorum yap

İleti!
Dave Byesmye Dave Byesmye
ይህን ጉድ ተሸክመህ ችግሩን በዘላቅነት መፊታትህ እንኳ በከፊልም የማያሰደስታቸዉ በእዉት የምሰሩትንና ለራሳቸዉ ለዉሸት ፖሌትካ ድንፋታዉን እየነፋ ዕድሜዉን ለማረዝም ይጥራል ግን ከዉሸት ጋር መቸም መጨማለቅ የለብንም
May 29, 2021, 00:57

~